የየሱስ ክርስቶስ መንገድ 

 

ሃይማኖት1) - ከየሱስ ክርስቶስ ጋር ስጓዙ - ሰዉን ከእግዚአብሔር ጋር እንደ "ማገናኛ ድልድይ"

 1) ሃይማኖት የሚለው ቃል መነሻው በላቲን ሪ-ሊጊዮ ሲሆን ትርጉሙም ከዉስጣችን ሆኖ በኛው ዉስጥ መልክ ከምይዘው ከእግዚአብሔር ጋር-እንደገና መገናኘት ማለት ነው። ይህም እንደ ሆሎግራም (በፎቶግራፍ ጥበብና በጨረር አማካይነት ሶስት ዓይነት ቅርፅ ያለው ፎቶግራፍ) በሰፊው ይከሰታል።

በሰብአዊ ፍጡር ሕይወት ውስጥ ያሉትን ጥልቅ ችግሮችን ማወቅ

ሰውነትን ከማዳን ባሻገር ላሉት ለውጦች ደግሞ የየሱስ የመጀመሪው ጥያቄ፡ "ልትድን ትወዳለህን?" (ዮሐንስ 5፡ 6) ነው፤ ወይም ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ ከፈለጉ፣አሁንም መለወጥ ያለብዎትን ጉድለቶች ያውቃሉ? አንድ ሰው ከቀላሉ የሕይወት ጉዳዮች በስተጀርባ ዘወትር ከሃይማኖት ጋር ግኑኝነት የሌላቸውን ማዕከላዊ የመገናኛ ክሮችን ሊያገኝ ይችላል። ጎልማሳ ለመሆን እያደገ ያለው ልጅ አዳዲስ ችሎታዎቸን ያዳብራል። ዳሩ ግን፣ ነገሮችን በፅናት ለመለማመድ የሚያስችሉት አንዳንድ የመጀመሪያዎቹ ችሎታዎች ይሰወራሉ። በኋላም አንድ ሰው እነዚህን የተፈጥሮ ችሎታዎች ለማደስ ይሞክራል። በዚህ ሁኔታ የሰው ደንዳናነት እየላላ ወይም እየጠፋ ሲሄድ፤ ተጨማሪ ችሎታዎች ግን ይቀራሉ። በአንጎልና በሕይወት መካከል ያሉት ክፍተቶች(ስብረቶች) - በ"ልብ" ውስጥ ባለው ደካማ ድልድይ፣ በአእምሮና በተፈጥሮ ሕይወት መካከል ወዳለው ክፍተት እያመሩ፣ እንደገና በተሻለ ሁኔታ ይቀናጃሉ። ይህ ክፍተት በጥንታዊው የገነቱ ታሪክ ውስጥ "መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ ስለመብላት" አንድ ትርጉም እንደሆነ ማሳየት ይቻላል። እናም "ካልተመለሳችሁ እንደ ሕፃናትም ካልሆናችሁ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም።" ያለው የየሱስ አባባል የተመሰረተው መመለስና መለወጥ በሚቻልበት ጥልቅ እውቀት ላይ የተመስረተ ነው(ማቴዎስ 18፡1-3፤ ማርቆስ 10፡15፤ሉቃስ 18፡17)። ይህም ሀፍረት እንደማይሰማችው ልጆች አዃኻን ዓይነት ብቻ ሳይሆን "ምሳሌያዊ" 2) ዋና የእድገት መሰረተ ሃሳብ ንድፎችን በተመለከት ነው ("ለሰው ጥቕም ትምህርት የሚሆን" የጠፋው ክፍል ማለት ነው)። ይህ መንገድ ከዛሬው ውስን የአእምሮ ንቃተ ሕሊና ባሻገር ይዘለቃል።

2) "ምሳሌያዊ" የ ሲ ጂ ጃንግና የሌሎቹ ጥልቅ የስነ አእምሮ ቃል ፤ የሰው ዘር የመኖር ገፅታዎች በተለያዩ መልኮችና ቅርፆች ለምሳሌ በሕልም ይገለጻል።  ዳሩ ግን ፣ " ዋና ተምሳሌያቱ " ደግሞ በከፍተኛ ደረጃ የተቀላቀለና አሳሳች ይዘት አለው። "እግዚአብሄር"ን እንደ ሽማግሌ አድርገው ያዩታል፣ እና " ሰማይ" ን እና "ገሃነም" ን "የማህበራዊ ህሊና " ተምሳሌያት አድርገው ይጠቅሱአቸዋል። ጃንግ ይህ በትክክል ምን እንደነበረ አላወቀም። ቢያንስ የዚህ የህሊና ደረጃ ማዕከል በተወሰነ ደረጃ በሁሉም ሰዎች የሚታይ ይመስላል - በሰዎች ውስጥ በተቀረጹት መልኮችና ሃሳቦች። እንግዲህ ፣ ይህ በሰው ዘር ታሪክ ውስጥ ከመጀመሪያ ጊዜ ጀምሮ እንደ ዋና ዓይነት መታሰቢያ ብቅ ይላል - እንደ " ጥንታዊ ሃይማኖት ህሊና " …..) ዘመናት በፊት እንኳን። ይህ የህሊና ደረጃ ደግሞ እንዲህ ዓይነት ተቃራኒ ነገሮችን ይይዛል - ሰዎች በህይወታቸው ሲለማመዱ ፣ ከመላ ጎደል " የሚታዩ " ተቃራኒ ነገሮችን ......) ። ቀረብ ብለን ስናይ እግዚአብሄርን በዚህ ዓይነት ማየቱ አስቸጋሪ ገለጻ ይገልጻል (...)። የፈጠራ ታሪኮች፣ በርግጥ ለልጆች ጠቃሚ ሊሆን ከሚችለው፣ ከዚህ የምልክታዊ ዓለም ጋር ፈጠራ ባለበት ሁኔታ ለመገናኘት ሞክረዋል። ዳሩ ግን ፣ አዋቂዎች ፣ ከነዚህ ምልክቶች አልፈው ሊሄዱ ሊሞክሩ ይችላሉ - በብዙ ሰብአዊ ገጽታዎች የሚገናኙ ምልክቶች። ዳሩ ግን ትክክለኛው ችግር ስለ እግዚአብሄር እነዚህ የውሸት ጽንሰ ሃሳቦች እንዲያቃስቱ ከማድረግ ይልቅ እግዚአብሄርን በቀጥታ መፈለግ ነው።

ይህም አንድ ሰው ይህንን ሁሉ በራሱ ጥረት ይቋቋመዋል ወይም ይችለዋል ማለት አይደለም። ይህንን ሁሉ በቁጥጥር ሥር ለማዋል የሱስ ትክክለኛውን መንገድ፣ኃይል ወይም ምህረት ያቀርባል። እውነትን የሚፈልጉ ክርስቲያኖች፣ ክርስቲያን ባለ ታሪኮችና ክርስቲያን ቀማሚዎች ወደ በለጠ (ፍፅምና) አቅንተዋል (5፡ 48፤ ዮሐንስ፤ 10፡ 34ን ያወዳድሩ) ። ሌሎች ብዙ ክርስቲያኖች በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ተመሳሳይ ልምድ አላቸው። በውስጣቸው ቢፈልጉም፣ በማህበራዊ ሕይወታቸው እምነታችውን ተግባራዊ ቢያደርጉም ወይም እኛ "ሙሉ ክርስትና" ብለን እንድምንጠረው ሁለቱንም ቢያጣምሩት ምንም አይደለም። ብዙ ሌላ ባህሎችም ለዛኛው ውስጣዊ ግጭቶች መፍትሄ ለማግኘት ሽተዋል፤ ለምሣሌ ያህል የታኦእስቶች ቀማሚዎችና አንዳንድ የዮጋ ትምህርት ቤቶች 3)

3) ዮጋ የሚለው የሕንድ ቃል፣ ቃል በቃል ሲተረጎም "በቀምበር አጥምደው" ማለት ከሥር ከመሰረትና ከዘላለማዊነት ጋር እንደገና ለመገናኘት መፈለግ ማለት ነው።

"እግዚአብሔር- ሰው" የሱስ ክርስቶስ፣ ‘አዲሱ አዳም’ ሰብአዊ ዘሮች ከዛ ጊዜ ጀምሮ የተሸፈነውን የቀድሞ በህርያቸውን መልሶ ማግኘት የሚችሉ ለመሆናቸው ምልክት ነው። በአሁኑ ሰዓት አደገኛ የሆኑትንና፣ የተሳሳቱትን በህርያትን ለማስተካካል ጊዜው ነው። የሱስ፣ ለምድር እንደ "ዕድለኛ እጣ"፣ ለሕይወት ትርጉም ቀዳሚው ምንጭ መገናኛ የሆነውን እግዚአብሔርንና በከፍተኛ ደረጃ ያደገውን የስው ንቃተ ኅሊና ወክሎአል። የመበስበስ ኃይሎችንም ተቋቋሞአል። ከሰዎች የተለየ ቢሆንም ቅሉ ደግሞ በተለይም ሰዎች ይህንን አውቀው ቢያደርጉ ማድረግ እንድችሉ ዘንድ የገለጠ ሰብእዊ ፍጡር ነው። ዳሩ ግን ስለ ታሪካዊዉ የሱስ ለማያዉቁት እንኳን ትንሳኤዉንም ጨምሮ ሕይወቱ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል። ይህም በሼልድሬክ ምርምር እንደተገኘው፣ አንድ ዓይነት እንስሳት በደሴታቸው ውስጥ በጋራ በሆነ የኃይል መስክ ተፅዕኖ ሳቢያ አንድ ዓይነት ነገር ከተማሩ በኋላ በሌላ ደሴቶች ውስጥ የሚገኙ እንደዚያው ዓይነት እንስሳት አንድ ነገር በፍጥነት ለመማር እንደሚችሉ ዓይነት ነው።

በመጀመሪያ ደረጃ ያለ ቤተክርስቲያን ከእግዚአብሔርና ከክርስቶስ ጋር ግንኙነት ሊኖር ይችላል፤ ዳሩ ግን፣ ተገቢ የሆነ የክርስቲያኖች ማህበረሰብ ጠቃሚ ነው። ተጻራሪ የስነ መለኮት ትምህርቶች ክርስቶስን እንደ መንፈሳዊ አማካሪ ወይም የማህበረሰብ ለውጥ አቅንቃኝ ብቻ አድርገው የሚያቅርቡበት ሁኔታዎች ከእንግዲህ ወዲህ የመጨረሻ አማራጭ ሊሆኑ አይችሉም። ዳሩ ግን፣ በተላይም አንዱ ከሌላው በተሻለ ሁኔታ የሚያውቅ ከሆነ ለአንድ ሰው ፍንጭ ይሰጣል። እያንዳንዱ ግለሰብ በግል ክፍሉ ሆኖ እራሱን ለክርስቶስ አስተካክሎ መስጠት ይችላል። ዳሩ ግን በመጨረሻ ደግሞ በገበያ ቦታ ሊሆንም ይችላል። ለዚህ ዓላማ አንድ ሰው በወንጌሎች የቀረቡትን የራሱን ባህርያት ማስታወስ ይችላል። ክርስቶስ ከሞት ተርፎ በትንሳኤ ድል እንዳገኘ የሚይይ ሰው ክርስቶስ በአሁኑ ሰዓት እየሠራ እያለ ሊገናኛው ይችላል።(ዘውትር ከክርስቶስ ውጭ ባሉበት ሁኔታ ሰዎች ከሞት ተርፈው የሚያቅርቡት ብዙ ምስክርናቶችም አሉ)። አንድ ሰው ሁሉን ነገር እንደሚይዝለት፣ ከራሱ ጋራ ለእግዚአብሔር እንደታላቅ ወንድም "በርሱ ስም" የጸሎት ስሜት ሊሰማው ይችላል (ለምሳሌ፣ ዮሐንስ 15፡16፤ ማቴዎስ 6፡ 7-15፤ ማቴዎስ 6፡ 18፡ 19-20)ን ይመልከቱ።

እግዚአብሔር፣ መሠረቴ፣ ረድኤቴና ተስፋዬ!
ከየሱስ ክርስቶስ ጋር በአንድነት ከአንተ ዘንድ ለምመጣልኝ ለሁሉም ነገር ይድረስህ ምሥጋናዬ**፤ እኔና ከአንተ አርቆኝ ለወሰደኝ ለሁሉም ነገር ይቅር እንድትለኝ እለምንሃለሁ፤ በዚህ በዝምታ፣ እባክህን በመንፈስህ ጠቢብ አድርገኝ***፤ በመንገዴ አንተ ሳበኝ

*) ማርያምን የማጠቃለል አዝማሚያ ያለው ሰው ይህንን ማድረግ ይችላል። በዚህ መንገድ የወንድና የሴት ባህርያት ደግሞ ጎልተው ይታያሉ።
**) ተጨማሪ ልምምድ መሆን የምችለው ደግሞ፡ በመጀመርያ እንደ ጭንቀት፣ ጥላቻ፣ ቁጣ፣ ግድየለሽነት፣ ከልክ ያለፈ ድፍረት፣ እጅግ በጣም ከባድ የሆነ ጥርጣሬን ወይም ችግሮችን የመሳሰሉትን አሉታዊ ስሜቶችን መመልከት ያስፈልጋል። እነዚህ ነገሮች በቃላት ወይም በአእምሮ ብቻ ሆነው እንደሆነ እንኳን ማቴዎስ 5፡22ን ያማሳክሩ። ሁለተኛ፣ እነዚህን ነገሮች ከማመንዠግ ይልቅ ነገሮቹ ምን እንደሆኑ በደንብ ለማወቅ እንድቻል ዘንድ መጠበቅ ያስፈልጋል። ሦሥተኛ፣ እነዝህን ችግሮች በፀሎት ለእግዚአብሔር አሳልፎ መሰጠት ተገቢ ነው። ከዚያም ባሻገር እንደዚሁም የራስን መላ ሕይወት በእግዚአብሔር ወይም በክርስቶስ እጅ አሳልፎ መስጠት ይቻላል። አራተኛ፣ አንድ ዓይነት እፎይታ እስኪገኝ ድረስ መጠበቅ ያስፈልጋል።
***) ፀጥታ "በደረሱብን ነገሮች ላይ እንድንረጋጋ"፣ መፍትሄ ለመሻት በተቻለ ሁኔታ እንድንዘጋጅ ወይም በፀሎት ላይ እንድንሆን ያደርገናል። ከዚያም አዲስ ለሚከሰቱብን ነገሮች የበለጠ ክፍት እንድንሆን ያደርገናል።

በዚህ መንገድ ላይ የሥነ ምግባር አስፈላጊነት

በመንገዱ አንድ ደረጃ፣ ከሁሉም በላይ የሆነውን "እግዚአብሔርን መውደድ"ና "ባልንጀራህን እንደ ራስህ መውደድ" (ማቴዎስ 19፡19) ነው። አንድን ሰው መውደድ ደግሞ አንዱ ለሌሎች ለሚያደርገው ተግባር የመፈለጊያ ጥረት አካል ሊሆን ይችላል። የራሱ ባህርይ በመሆኑ፣ፍቅር ከጥበብ ጋር በመቀላቀል ሰውን ከክርስቶስ ጋር ሊያገናኝ ይችላል። የመልካም ተግባሮች መንገድ ደግሞ ከሚያመጣቸው ለውጦች ጋር የክርስቲያንን መንገድ ግልጽ ያደርገዋል። የሱስ የቀድሞውን የመልካም ሥነ ምግባር መሠረተ ሀሳቦችን ጠብቆአል፤ ምክንያቱም፣"ሰው [ዘውትር] የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና"( ገላትያ 6፡7)፤ ዳሩ ግን፣ እርሱ ከውጫዊው ህግ ይልቅ በግለሰብ ኃላፊነት ላይ አትክሮአል። በውስጣችን አንድ ነገር እንዳለ አንድ ሰው ሊያስተውል ይችላል፤ ለምሳሌ፣ ክርስቶስ በራሱ ሕይወት ምሳሌ ሆኖ እንዳሳየው፣ ከመንፈሱ ጋር ተስማሚ በሚሆን መንገድ ክፋት ወይም ደግነት መኖሩን ማወቅ ያስፈልጋል። ይህ ነገር በአንድ ግለሰብ ልብ፣ ነፍስ ወይም መንፈስ ውስጥ ይንፀባረቃል። በተቻለ መጠን፣ ዘወትር የክርስቶስን የታወቁትን ባህርያት የራስ ባህርይ ማድረግ ጠቃሚ ነው። ለጊዜው ትላልቅ ለውጦች ባይከሰቱም ቅሉ፣ ከርሱ ጋር የጠበቀ ግኑኝነት ይፈጠራል።

በዚህ ሁኔታ በምህረት የሚመነጨው ኃይል፣ እንደገና ከ"ውጫዊው" ክርስቶስና እግዚአብሔር የሚቀርበውን ሁለንተናዊውን የማዳን ኃይል ይስባል። እዚህ ላይ ደግሞ የያንዳንዱ ሰው የመለማመጃው መንገድ የተለያየ ሊሆን ይችላል። ዳሩ ግን፣ በዚህ ሁኔታ በአንድ ሰው ላይ የሚመጣው ለውጥና ነገሩ የሚከሰትበት ሁኔታ በጥልቀት ሊሆን ይችላል። ጥቂት "ቅዱሳን"ንና "ረቂቅ በሆነ መንገድ ከአምላክ ጋር የሚገናኙ" ሰዎች ከዚህ ቀደም የቀሰሙአቸው ልምዶች በኛው በ"ጥፋት " ዘመን በተራ ሰዎች አማካይነት ይሰራጫል። አንድ ሰው ጠቃሜታውን ወዲያውኑ ሊገነዘበው ስለማይችል፣ ይህ ሃሳብ እዚህ ጋ መጠቀስ አለበት። ነገሩ የሚያሳስባቸው ሰዎች ይህንን ለዋጭ ኃይል መቀበል አለባችው፤ አለበለዚያ እንደ አንድ ዓይነት "ፍርድ" እንዲሰማቸው ከርሱ ጋር ተስማሚ የሆኑትን ባህርያት ያላጎለበቱትን ሰዎች መሰናክሎች በአሰቃቂ ሁኔታ ይመታል።

ወደ አንተ የሚሄዱትን፣ ሌሎችን እንዳላሰናክል አንተ ምራኝ፤ እንደ ፈቃድህ ሌሎችን እንድረዳ ዘንድ አንተ ምራኝ በመንገዴ አንተ አድነኝ* በፍቕርህ እንድጓዝ እርደኝ

*) እዚህ ጋ ሌሎችም አባባሎች ሊጨመሩ ይችላሉ።

ከጥንት፣ታሪክ ካልተጻፈበት ዘመን ጀምሮ በባህሎች ውስጥ ያለው ሰፊው ተመሳሳይ የዕድገት ደረጃ

ከልጅነት እስከ ጎልማሳነት እንዳለው የዕድገት ደረጃ፣ እንዲሁም የሰው ባህሎች በተለያየ የንቃተ ህሊና ደረጃዎች አልፈዋል። በአንዱ በኩል አዳዲስ ችሎታዎች (ፈቃድ፣ ከድሮ ይልቅ በአሁኑ ዘመን ሰው ሃሳቦቹንና ስሜቶቹን የመግለጽ የበለጠ ነጻነት አላው) ሲከሰቱ በሌለው በኩል ደግሞ በችግር ውስጥ በሚከት ሁኔታ ከመለው "ተፈጥሮ" ጋር ያለው ቅርበት ዋጋ አጥቶአል (ለምሣሌ፤ ጂን ገብሰር፣ በጀርመንኛ " ኡርስፕራንግ ኣንድ ገገንዋርት"፤ "አሮጌ"፣ "ጠንቋይ"፣ "ረቂቅ"፣ ምሁር ንቃተ ህሊና እያሉ የማመዛዘን አመለካከት አለ። ከዚያ ባሻገር የተሻላና የተቀናጀ ግምታው ሃሳብ ሊመነጭ ይችላል። ተዋቂ ሰዎች እንደዚሁ እያደጉ የሚሄዱት ደረጃዎች ለባህሎቻቸው ፍሬያማ እንዲሆኑ ረድቶአቸዋል። ይህ የሆነውም ብዙ መሰናክሎችን አልፎ፣ ዳሩ ግን በፊት እንደተጠቀሰው የከረሙትን ችሎታዎች አክስሞ ነው። በአሁኑ ታሪክ፣ ስዎች ለመኖር ከፈለጉ ትንሽ ሆነ ትልቅ አዝጋሚ ለውጦችን የበለጠውን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የተደቀነባቸውን ፈተና መጋፈጥ አለባቸው4) ። ከእ ኤ አ 2000 ዓ ም አካባቢ ጀምሮ ይህ የሚቻል ነገር ነው። ይህ ዕድገት እንደ አእምሮ ያሉትን የቀድሞ ወይም አሮጌ ባህርያትን ማበላሸት ወይም መቀነስ አይገበውም። በቂ ግለሰቦች የበለጠውን ምሉዕ የሆነ የተለምዶ አስተሳሰብ ቢያጎለብቱና፣ ከመለኮታው ሥር መሠረታቸው1) ጋር ያለውን ግኙኝነታቸውን ቢያሳድሱ፣ ሰብአዊ ፍጡር "ከላይ" ዕርዳታ በማግኘት በ"መጨረሻው ዘመን" ከሚመጠው ጥፋት ጋር ያለውን ውድድር ሊያሸንፍ ይችላል። ይህ ደግሞ በዓለም ላይ እንደ ሰላም እንቅስቅሴ ከመሳሰሉት ጋር ግኑኝነት አለው፤ ሁሉም በጎ ፈቃድ ያላቸው ሰዎች የግድ በ"ጨዋታው" ላይ ሚና አላቸው። በርካታ ሰዎች በቀጥታ ተቋቁመው ባሉት የሃይማኖት ትምህርት ቤቶች መስመር ይህንን በግልጽ እየፈለጉት ነው። አንዳንድ "መሃል ሰፋርነት" ሊኖር የሚችል ቢሆንም ቅሉ፣ ያለፈውን ነገር በማስረሳት እገዛ እያደረጉ ወደፊት ይገሰግሳሉ። አንድ ሰው ምንም ያስብ ምንም፣ ዓላማው የሰውን ዘር "ማዳን" ወይም በንቃተ ህሊና መሻሽል ነው። የቀድሞ "መርሃ ግብር" ወዴት እንደሚመራ በግልጽ የሚታወቅ በመሆኑ ዘመናዊ የስነ ምግባር ደረጃዎች መለወጥ አለባቸው። ማንኛውም ነገር የሙሉ ነገር አካል ነው፤ እንዲሁም ሁሉም በጎ ነገሮች ዓለምን ይጠቅማሉ።

በሄርበርት ግሩህል በመጨራሻው መጽሐፉ ውስጥ በጀርመንኛ አባበል፣ "Himmelfahrt ins Nichts" ፣ (ትርጉሙም ወደ ባዶ ሥፍራ ማርጋት)፣ አንድ ሰው የተረሳው የኃይልና የዕድገት ምንጭ ይኻውም ዕድል ብቻ (እግዚአብሔርን ለማለት ነው) በሀሳቡ ይመጣበታል እንደሚለው፣4) እኛ በተስፋ አስቆራጭነት አመለካከት አንስማማም፤

ሰዎች ሞትንና ሕይወትን የተመለከቱበትን ዉሳኔዎች በአንተ እጅ ይጥሉ ዘንድ በመንፈስህ አነሳሳቸው* ለተፈጥሮህ የሚሠሩትንም እርዳቸው*** ይህን ዓለም ተስፋ ወደሰጠሃው ወደ አዲሱ ዘመን ዘልቆ ይገባ ዘንድ ምራው**

*) እዚህ ጋ ዝርዝሮችም ሊጨመሩ ይችላሉ፤ ወይም ‘ሁከትን መካብ ማቆም’፣ ችግሮችን በማቃለል አንድ የሁከት መንስኤ ማስወገድ’፤ ሰላማዊ ሰዎች ሰብአዊ መብታቸው ተከብሮ ለመኖር የሚያስችላቸውን የደህንነት እርምጃችን ብቻ ተግባራዊ ማድረግ’ ’ታዋቂ ከሆኑ ከተለያዩ የሃይማኖት ሰዎች ጋር ውይይት ለመጀመር፣ ከመሳሰለው ፀሎት በኋላ በአማላጅነት ሊገባ ይችላል…. **) ሉቃስ 11፡2፤ 21፡31። ራዕይ 11፡ 6፤… እግዚአብሔር ለርሱ የተሰጠውን ፍቅር ያከፋፍላል።

በትንሹ ሆነ በሰፊው ወደ እግዚአብሔር "መመለሻው" ቅርብ ነው።

ዮሐንስ 1612-13: " 12. የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ፥ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም። 13. ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።"

 

ወደ ways-of-christ.net/am ዋና ገጽ:

ዋናው ጽሑፍ ከተጨማሪ ዐርዕስቶች ጋር (በእንግሊዝኛ):

የየሱስ ክርስቶስ መንገድ፣ እርሱም ለሰብአዊ ፍጡር ልቦና፣ የሰውን ዘርና ምድሪቱን ለመለወጥ የሚያደርጋቸው አስተዋፅዖዎች፤ በበርካታ ምርምርና ልምድ ላይ የተመሠረቱ አዳዲስ አመለካከቶችን በማፍለቅ የግል ባህርይን ዕድገት ለማጎልበት ተግባራዊ የሆነ ጥቆማን የሚሰጥ ገለልተኛ የሆነ የመረጃ ምንጭ ነው።

"የክርስቶስ መንገድ" ድረ ገፅ የምርምርና የጥናት ፕሮጀክት ነው። "የክርስቶስ መንገድ" በሃይማኖቶች መካከል ሰላማዊ ግኑኝነቶችና ጥልቅ መግባባት እንዲኖር ድጋፍ ይሰጣል። "የክርስቶስ መንገድ" ከቤተ ክርስቲያናትና ከሌሎች ድርጅቶች ገለልተኛ ሆኖ ትርፍ ወይም የፖለቲካ ሥልጣን ለማግኘት ጥረት አያደርግም። "የክርስቶስ መንገድ" የሃይማኖት ስብከት እያደረገ ወይም አባላትን ለመሰብሰብ ዘመቻ እያካሄደ አይደለም ያለው።