Problems? Download fonts      PDF

የየሱስ ክርስቶስ መንገድ

+

የሱስ ክርስቶስ

የየሱስ ክርስቶስ መንገድ፣ እርሱም ለሰብአዊ ፍጡር ልቦና፣ የሰውን ዘርና ምድሪቱን ለመለወጥ የሚያደርጋቸው አስተዋፅዖዎች፤ በበርካታ ምርምርና ልምድ ላይ የተመሠረቱ አዳዲስ አመለካከቶችን በማፍለቅ የግል ባህርይን ዕድገት ለማጎልበት ተግባራዊ የሆነ ጥቆማን የሚሰጥ ገለልተኛ የሆነ የመረጃ ምንጭ ነው።

በዚህ በአማርኛ ቋንቋ በተጻፈው ገፅ ከፀሎት ጋር ለተያያዙት ጉዳዮች መሠረታዊ የሆኑ ጥቆማዎችን ያገኛሉ።

.

  ሃይማኖት - ከየሱስ ክርስቶስ ጋር ስጓዙ - ሰዉን ከእግዚአብሔር ጋር እንደ ማገናኛ ድልድይ 1)

መረጃ፦ የሱስና እስልምና 1)

 በአንዳንድ ቋንቋዎች 2) ደግሞ በአጠቃላይ ከወንጌሎችና ከዮሐንስ ራዕይ ጋር አጠቃላይ የሆኑ ሐተታዎችን የያዙ በሌሎች ብዙ ዐርዕስቶች ላይ የተጻፉትን ጽሑፎች ያገኛሉ3)

.

 1) አጫጭር ትርጉሞች፡ 

2) አጠቃላይ ትርጉሞች እንግሊዘኛ እና ጀርመንኛ ዘወትር ይሻሻላሉ ,  ፈረንሳይኛ (français) ፈረንሳይኛ ደግሞ፦

  -  

http://www.ways-of-christ.com/am

ለሰላም ለሕይወትና ለምድር የሚጸለይ ፀሎት

ይህ ፀሎት ደግሞ ውጤታማ ወደ ሆነው ፀሎት ሊመራ የሚችለውን፣ የክርስቲያንን አመለካከት "ያንፀባርቃል።"

እግዚአብሔር፣ መነሻዬ፣ ረድኤቴና ተስፋዬ! ከየሱስ ክርስቶስ ጋር በአንድነት ከአንተ ዝንድ ለምመጣልኝ ለሁሉም ነገር ይድረስህ ምሥጋናዬ እኔና ከአንተ አርቆኝ ለወሰደኝ ለሁሉም ነገር ይቅር እንድትለኝ እለምንሃለሁ በዚህ በዝምታ፣ እባክህን በመንፈስህ ጠቢብ አድርገኝ

ወደ አንተ የሚሄዱትን፣ ሌሎችን እንዳላሰናክል አንተ ምራኝ እንደ ፈቃድህ ሌሎችን እንድረዳ ዘንድ አንተ ምራኝ በመንገዴ አንተ አድነኝ*

ሰዎች ሞትንና ሕይወትን የተመለከቱበትን ዉሳኔዎች በአንተ እጅ ይጥሉ ዘንድ በመንፈስህ አነሳሳቸው** ለተፈጥሮህ የሚሠሩትንም እርዳቸው*** ይህን ዓለም ተስፋ ወደሰጠሃው ወደ አዲሱ ዘመን ዘልቆ ይገባ ዘንድ ምራው****

*) እዚህ ጋ ሌሎችም ሊጨመሩ ይችላሉ። **) እዚህ ጋ ዝርዝሮችም ሊጨመሩ ይችላሉ፤ ወይም ‘ሁከትን መካብ ማቆም’፣ ችግሮችን በማቃለል አንድ የሁከት መንስኤ ማስወገድ’፤ ‘ሰላማዊ ሰዎች ሰብአዊ መብታቸው ተከብሮ ለመኖር የሚያስችላቸውን የደህንነት እርምጃችን ብቻ ተግባራዊ ማድረግ’፤ ’ታዋቂ ከሆኑ ከተለያዩ የሃይማኖት ሰዎች ጋር ውይይት ለመጀመር ‘፣ ከመሳሰለው ፀሎት በኋላ በአማላጅነት ሊገባ ይችላል….በማቴዎስ 5፡ 9 ና 26፡ 52 ያለውን ማየት ይችላሉ።

***)ተፈጥሮ ለርዳታ እሪ ትላለች።ጊዜው የፅሎት ነው፡ ጌታ ሆይ ‘ክተነሳሳብን’ የተፈጥሮ ኃይል አድነን። ዳሩ ግን ይህ ከሌላው ተፈጥሮ ጋር ካለው ግንኙነት አኳያ የሰውን የባህርይ ለውጥ አይተካም።

****) ሉቃስ 11፡2፤ 21፡31። ራዕይ 11፡ 16፤… ለመፀለይ በአንድ"መንፈስ" በመሆን በአንድነት ለመኖርና ተግባራችንን ለማከናወን እንችል ዘንድ እግዚአብሔር በሁሉም ቤተ ክርስቲያናት ለርሱ የተሰጠውን ፍቅር ያከፋፍላል።

 

3) እዚህ የተጠቀሰው ዋና ጽሑፍ በሌሎች ቋንቋዎች የሚከተሉትን ምዕራፎች ይይዛል፦-ክፍል 1- የአማላጅነትን ፀሎት ጨምሮ በሥርዓት የተዘጋጁት ጥቆማዎችና የዚህ ጽሑፍ ዓላማና ጠቃሜታ መግቢያ "መጀመሪያ ቃል (በግሪክ ሎጎስ) ነበረ… እናም ቃሉም ሥጋ ሆነ"፤ የናዝሬቱ የሱስ፤ ልደቱ፤ የክርስቲያን ዳግመኞ ልደትን በተመለከተ ተጨማረ ገፅ፤ በየሱስ የወጣትነት ዕድሜ ወቅት የሚገኝ ጠቃሚ ነገር አለ ወይ ? ፤ "የሱስ ተብለው በሚጠሩ በሁለት ልጆች" መካከል የተከሰተ ጥላቻን በተመለከተ የቀረበ አስተያየት፤ በመጥመቁ ዮሐንስ በዮርዳኖስ ወንዝ የተከናወነ ጥምቀት፤ የዛሬውን ጥምቀት በተመለከተ ከተጨማሪ ማብራሪያ ጋር ይቀረበ ተጨማሪ ገፅ፤ በበረኃ ውስጥ ፀጥታ፤ ፈተናዎች፤ በቃና ዘገሊላ የተደረገ ሠርግ፤ (ወሲብ፣ የሌላውን ስሜት መካፈል፣ ማፅናናትንና ፍቅርን በተመለከተ የቀረበ አመለካከት)፤ "ቅዱስ ቅንአት" (ስሜቶችን በተመለከተ የቀረቡ አመለካከቶች)፤ የተራራው ላይ ስብከትና አእምሮን በተመለከተ የቀረቡ አመለካከቶች፤ በታቦር ተራራ ላይ የክርስቶስ መልክ መቀየር፤ አልአዛርን ከሞት በማስነሳቱ "ታአምራት" ላይ የቀረቡ ጥያቄዎች፤ "በጎች"፤ የክርስቶስ "የእግር እጥበት" እናም የቢታንያው ማርያም የሱስን መቀባት (ለክርስቲያን መንፈሳዊነት ጠቃሚ ነጥብ)፤ የመጨራሻው እራት፤ በድል መግባትና ግርፋት፣ የእሾህ አክሊል መደፋት" ና የመጨረሻው ንግግሮች፣ ስቅለቱና ቀብር (ከክርስትና ሃይማኖት ከቀረበ አስተያየት ጋር)፣ የባዶ መቃብር፣ ወደ "ሥዖል መውረድ" ና ወደ "ገነት እርገት" ጥያቄ፣ ትንሣኤ፣ "የክርስቶስ እርገት"፤ ጴንጤቆስጤ፣ የየሱስን ገፅታ በተመለከተ የቀረበ ጥቆማ። ክፍል 2፦ የቅዱስ ዮሐንስ ራዕይ፣ ትንቢቶች እንዴት እንደሚመረመሩ፣ የዮሐንስ ራዕይ ማውጫ፣ ሰባቱ ቤተክርስቲያናት፣ የዛሬ ቤተክርስቲያናት ልዩነታቸውንና አንድ ለመሆን ያላቸውን መንገድ በተመለከተ የቀረበ ተጨማሪ ገፅ፣ "ሰባቱ ማህተሞች"፤ "ሰባቱ መለከቶች"፤ "ሰባቱ ነጎድጓች" ና ሁለቱ ነቢያት፣ ሴቲቱና ዘንዶው፣ ከባህር ውስጥ የሚወጣ "ሰባት ራሶች ያሉት አውሬ"፣ ከምደር ላይ የሚወጣ "አሥር ቀንዶች ያሉት አውሬ"፣ "ሰባቱ የቁጣ ጽዋዎች" ና የ "ባቢሎን" መጨረሻ፤ የክርስቶስ ደግመኛ መምጫ፤ (ትክክለኛው) "የሺህ ዓመት ሰላም"፤ አዲስ ሰማይ፣ አዲስ ምድርና "አዲስቷ ኢየሩሳሌም"፤ የመጨረሻ ምዕራፍ ፦ የክርስቲያን አመለካከት፣ ሠንጠረዥ፤ በዓለም እየሆኑ ከዓለም አለመሆን፣የክርስቲያኑ አመለካከት። 3፡ ሌሎች ዐርዕስቶች፦ ፀሎት፣ የሥነ ምግባር ዋጋዎች መሠረተ ሃሳብ፤ ዘመናዊ የየሱስ ማለምት ማስተካከያ፤ የሱስ፣ የሰው ምግብና እንስሣትን መጠበቅ፣ ሳይንሶችና በእግዚአብሔር ማመን፣ የሱስና ፈውስ - ዛሬም ቢሆን፣ በረከቶች፣ ክርስቲያን ለምጣኔ ሃብትና ለማህበራዊ ጥያቄዎች ያለው አመለካከት፣ ክርስቲያን ለማሀበረሰብና ለፖለቲካ ያለው አመለካከት፣ ሃይማኖትና ፍልስፍና፣ በሃቤርማስ ንግግር ላይ የተሰጠ አስተያየት፤ ያልተወለደ ፍጡር፤ እነዚህ ገጾችና ትምህርት የተለያዩ የክርስቲያን ስነ መለኮት አመለካከቶች፤ የክርስቲያን ተማህፅኖ፣ ማነቃቂያና ቤተ ክርስቲያናት፣ ከሞት በኅላ ስላለው ሕይወት ስላለው ጥያቄና ከሞት በፊት ባለው ሕይወት ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ስላለው ያለው አመለካከት፤ ክርስቲያንነት - ሌሎች ስለ "ዕድል" እና "እንደገና መፈጠር"ን በተመለከተ ከሚያስተምሩት ከሌሎች ትምህርቶች ጋር ያለው ግኑኝነት፣ 4. ብሉ ኪዳንና እርሱ ከሌሎች ሃይማኖቶች ጋር ለመወያየት የሚያበረከተው አስተዋፅዖ፦ ብሉይ ኪዳን፣ የአይሁድ ኃይማኖትና የሱስ፤ "የሱስና እስላም"፣ የዛራታስትራ (ፓርሥስም) ሃይማኖት፤ "ቡዳዊነት" ፣ "ሂንዱአዊነት"፣ "ታኦዝምነት"፣ኮንፍስካዝምነት"፣ ሽንቶዝምነትና የተፈጥሮ ኃይማኖቶች፣ ሃይማኖት ሰውን እንደገና ከእግዚአብሔር ጋር "የማገነኛ ድልድይ" ።

የባለቤትነት መብት፡ በዚህ ገፅ ያሉትን ጽሑፎች፡ ያለምንም ለውጥ፡ አትመው ልወሰዱ ወይም ለወዳጆች ሊያቃብሉ ይችላሉ!

ኢ ሜይል፡ እባክዎን በእንግሊዘኛ ወይም በጀርመንኛ


መጽሐፍ ቅዱስ