የየሱስ ክርስቶስ መንገድ


 የተሻሻለ 

መረጃ፦ የሱስና እስልምና

በተለያዩ የሃይማኖት ድርጅቶች መካከል ያለው ውይይት.
ይህ ገጽ - ለብዙ ዓመታት እየተደረገ እንዳለ በተሻለ ሁኔታ ለመረዳትና በሃይማኖቶች መካከል ላላው ውይይት አስተዋፅዖ ነው። ይህ ገለጻ መለውን እስላም በተወሰነ ፈርጅ ለመመደብ አይሞክርም። በእስልምናም ቢሆን የተለያዩ አመለካከቶች አሉ. 

ቁርአንና ሌሎች "የመጻሐፍቱ ሃይማኖቶች"

እስልምና ማለት "ለእግዚአብሔር ፈቃድ እራስን አሳልፎ መስጠት" ማለት ነው።

የእስልምና ቅዱስ መጽሐፍ፣ ቁራን (ቁርዓን) በክርስትናም፣ ሊቀ መልአኩ ገብርኤል መሆኑ ተለይቶ በሚታወቀው በጅብሪል አማካይነት፣ ለነብዩ መሐመድ (ሙሐመድ) የተላለፈ መለኮታዊ ሀሳብ እንደሆነ ይታመናል። በእርግጥ ቅዱስ ቁርአን ከእስልምና መጻሕፍት ሁሉ የበለጠ ጠቃሚ መጽሐፍ ተደርጎ መወሰድ አለበት። ተጨማሪ ወጎች ("ሱና"፣ በተለምዶ፡ "ልምድ) ከነብያት አባበሎች ጋር ቁርአንን ለመተርጎም አንድ ሚና አላቸው። ነቢይም ቢሆን፣ በግል ባህርይው፣ ሰው እንጂ አግዚአብሔር አይደለም። በርካታ ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱሳቸውን በደንብ እንደማያውቁት ሁሉ ቅዱሳት መጽሐፍቶቻቸውን የማያውቁ እስላሞች እንዳሉ ደግሞ መገንዘብ ይገባል።

ቅዱስ ቁርአን ክርስቲያኖችንና አይሁዶችን አንዳንድ ጊዜ በቀጥታ "እናንተ የቅዱሳት መጻሕፍት ሰዎች" (ለምሣሌ ሱራ 4፡171) እናም "እናንተ የእሥራኤል ልጆች" ብሎ ይጠራቸዋል። ሆኖም ግን አብዛኛዎቹ ለዚህ ጉዳይ ቦታ ባይሰጡትም ቅሉ፣ ስለዚህ እነርሱ በዚህ ቅዱስ መጽሐፍ ውስጥ በተጻፈው ነገር ፍላጎት ሊኖርባቸው ይችላል። ቢሆንም ቅሉ የሃይማኖት ሳይንስ ሁሉንም ሃይማኖቶች ያጠናል- ከሁሉም ነገሮች መካከል፣ የአተረጓገማቸውን ታሪካዊ ዕድገት ያጠናል። ዳሩ ግን፣ ቅዱሳት መጻሕፍት በአክብሮት መጠናት አለባቸው። ከቁርአን ተቺዎች አንዱ ክፍል እንዲሁ ብሎን ጽፎአል፦ ዋና ቁርአን በእግዚአብሔር በጥሩ ቦታ ተቀምጦአል- ለንጹህ መላዕክት ንጹህ ነቢያት ብቻ ይቀርቡታል፤ ከነርሱ ሌላ ክፍል እንደዚህ ብሎ ይተረጎማል፣ በምድር የቁርአን አንባቢ ንጹህ መሆን አለበት።

ነብዩ፣ ነብያት በሚፈለጉበት ጊዜ፣ ለጊዜው (ወይም በመካከል ላለው ጊዜ) የተላከ እንደሆነ ተደርጎ ይታያል (ሱራ 5፡19*)። ቅዱስ ቁራን በነብዩ መሐመድ ትምህርቶች "አማኞች"ን፣ የቅዱሳት መጽሐፍት ሰዎችን" ና "አማኞች" ያልሆኑትን ለይቶ ያስቀምጣል። የ "ቅዱሳት መጽሐፍት ሰዎችን" ከ እስላሞች ሌላ በአንድ ወጎች ላይ የተመሠረቱትን በተለይም አይሁዶችንና ክርስቲያኖችን እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ዞሮአስትሮችን ወይም ፓርስዎችን ያጠቃልላል (ፓርሲስ፤ ሱራ 22፡17*)። ቁራን ስለ አንድ እግዚአብሔር፣ ከዚህ በኋላ ላለው ስለ መጨራሻው ፍርድ፣ ስለሕዝቦቻቸው ወይም ስለዘመናቸው ፀሎት የሚያደርጉትን በሁሉም የደረጃ ተዋረድ ያሉትን ነብያት ይቀበላል (ለምሣሌ፤ ሱራ 6 ፤ 83-92፤ሱራ 7፤ሱራ 4፤ 136*)። የነዚህ ሃይማኖት ሰዎች በጋራ መሠረተ ሐሰቦች እስካመኑ ድረስ፣ ቁራን እራሱ አማኞች ያልሆኑ ብሎ አይጠራቸውም (ለምሳሌ ሱራ 5፡48*)። በእስልምና የመጀመሪያ ምዕተ ዓመታት ክርስቲያኖችና አይሁዶች ወደ እስልምና እንዲመለሱ አልተገደዱም- በቁርአን ትምህርት መሠረት ፣ " በሃይማኖት ግዳጅ የለም"፣ ሱራ 2፣256። 
አብርሃም በአንድ እግዚአብሔር ማመንን ከመሰረቱ ፣ ለምሳሌ እንደ አንዳንድ መናኞች ከ"ሐኒፎች" እንደ አንዱ ይታያል።

"አላህ" ከቅድመ እስልምና አረብኛ "አል እላህ"- እንደ ሴማውያን ቃል ሆኖ፣ ከመለ ጎደል በእርግጥ ከሆነው በሙሴ መጻሐፍት የእግዚአብሔር መጠሪያ ስሞች አንዱ ከሆነው በዕብራይስጥ ኤሎሄም ጋር አንድ ዓይነት መነሻ አለው።

"አማኝ ያልሆኑት " - በአጠቃላይ፡ "ሸፋኝ" - በትክክለኛ ስሜት ብዙ አማልክት አምላኪዎች - መሐመድ በአረቢያ እንደተዋጋና መጽሐፍ ቅዱስ ለክርስቲያኖችና ለአይሁዶች ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው፣ ጣዖት አምላክዎች ናቸው። ዛሬ በሰፊው በአንድ እግዚአብሔርና በመጨራሻ ፍርድ የማያምኑትንና እስልምና አማኞች እንዳልሆኑ ያያቸዋል። አንዳንድ ጊዜ ቃሉ ሁሉንም እስላም ያልሆኑትን በውሸት ያጠቃልላል፤ አንዳንድ ጊዜ እራሳቸው እስላም ሆነው ልዩ አመለካከት ያላቸውንም ያጠቃልላል።

የሱስ ክርስቶስ በቁርአን

እዚህ ጋ መገንዘብ ያለብን ነገር፣ ቁርአን የሱስን እንደ ነብይ፣ ከእግዚአብሔር የተላከ ነብይ፣ ያለምንም ትርጉም የእግዚአብሔር "ቃል"፣ እናም እንደ "እግዚአብሔር መንፈስ"፣ (ሱራ 4፣171*፣ "እንደ አዳም የተፈጠረ" (ሱራ 2፣ 3 ፣ 5*….) አድርጎ ይቀበለዋል። ይህም አንዳንድ ዘመናዊ የክርስትና ሥነ መለኮት ሊቃውንት የሱስን የማህበራዊ ለውጥ አምጭ ብቻ አድርገው ከሚቀበሉት በላይ ነው። ክርስቲያኖች በመሐመድ ጊዜ ይህንን በአካል ገምተውታል (የሱስ እንደ እግዚአብሔር ልጅ ብቻ ነበር የሚታየው)። በኋላ የመጣው የሦሥቱ ሥላሴ ህገ ፅንሰ ሀሳብ በቁራን ተቀባይነት አላገኘም። ከአንድ ጋ መጥቶ መረጃ የሚፈልግ ሰው ሊረዳው እንደሚችል እንደ "እግዚአብሔር ቃል" (ዮሐንስ 1) አድርጎ በእውነት የሚያስረዳ ሰው በዛ ዘመን በቀላሉ አይገኝም ነበር (ለምሣሌ፤ ሱራ 6፣ 101)።
በሮሜ 1፡4፣ የሱስ በራሱ መንፈሳዊ ኃይል እንደ "ልጅ" ተተከለ ይላል- እናም እንግዲህ አልተወለደም።
እግዚአብሔር አይወለድም፤ የሱስን ፈጠረው እንጂ "አልወለደውም" ከሚለው ከእስልምና እምነት ጋር ክርስቲያኖች ሊስማሙበት ይችሉ ይሆናል። በተጨማሪም በግሪክ ቃል "ሎጎስ" የሚባለው የሱስ ለመለኮታዊ መነሻነቱ ወይም የየሱስ ክርስቶስን ተልዕኮን ለማመልከት የሚጠቀሙበት ቃል ነው። ይህም በቁርአን የሱስ የተባለው በወንጌል "ቃል" ተብሎ ነው የተተረጎመው። የቁርአን ጽሑፎች በሙስሊሞች ወይም በክርስቲያኖች ገና ሙሉ በሙሉ ያልተስተዋሉትንና በቃላት ምክንያት ጥቅም የሌለውን ጥላቻ የሚያስከትሉቱን ሚስጥሮች ይዘዋልን? አንዳንድ ከአንድ በላይ አምላክ መኖሩን እንደሚያሚኑት ሰዎች፣ መረዳት እንደምገባን ደግሞም ክርስቲያኖች ይህንን ትምህርት በቃላት ሲናገሩ እንደ የሱስ ትምህርት አይደለም የሚያስተምሩት። "ወደ (እግዚአብሔር) በእኔ ስም ፀልዩ ። ይህም ማለት ከየሱስ ትምህርት ጋር ስናስተያየው ነው ( ዮሐንስ 15፡16)። በየሱስ ሕይወት የሱስ ራሱ ሰዎችን ሊመራቸው በሚችለው በአንድ እግዚአብሔር ዙሪያ ነው የሚሽከረከሩት።

ሎጎስ (በበግሪክ፣ በዮሐንስ ወንጌል፣ እዚህ ጋ ከክርስቶስ ጋር የተያየዘው፣ "የእግዚአብሔር ቃል") በፓሬት የጀርመን ትርጉም፣ ከየሱስ ተለይቶ ነው የተቀመጠው። ሌሎች የቁርአን እትሞች እንደ እግዚአብሔር "ጉዳይ" ወይም እንደ እግዚአብሔር "ትዕዛዝ" አድርገው ያስተውሉታል (ሱራ 13፤12፤ ሱራ 11*)።

ቁርአን የሱስን "እንደ አዳም" ከአፈር የተፈጠረ አድርጎ ይመለከተዋል (ሱራ 3፡ 59*)፤ እናም የሱስ እንዲወለድ ዘንድ ከእግዚአብሔር መንፈስ ዘንድ መልዕከተኛ መላኩን ይናገራል (ሱራ 19፣17-22*)። የክርስቲያኑም በኩል መልአኩ ለድንግል ማርያም የሱስ ከመንፈሰ ቅዱስ እንዲወለድ ዘንድ ከእግዚአብሔር መንፈስ መላኩን ይናገራል። በተጨማሪም፣ የሱስ በመንፈስ ቅዱስ/ በቅድስና መንፈስ ብርታት እንዳገኘ ይገልጻል (ሱራ 5፣110*)። የየሱስን ሕይወት በተመለከተ መንፈስ ቅዱስም ተጠቅሶአል (ሱራ 5፡110)። 

እንደ ቁርአን አባባል ወጣቱ የሱስ ትንሣኤውን አብስሮአል (ሱራ 19፡ 33*)። ዳሩ ግን እዚህ ጋ፣ በቁርአን ዘወትር እንደተጠቀሰው በፍርድ ቀን ስለሚሆነው ስለ አማኞች ትንሣኤ ሊሆን ይችላል (ከዚህ በታች ሱራ 4፡159 የተጠቀሰውን ይመልከቱ)። ቁርአን የሱስ ሳይሞት ወደ ሰማይ በእግዚአብሔር ተወሰደ ይላል (ሱራ 4፡ 157-፤ሱራ 3 ፡ 55*)። 
የሱስ ወደ ሰማይ ከማርጋቱ በፊት መሰቀሉን፣ መሞቱንና ሞትን ድል መንሳቱን በተመለከተ ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች አይስማሙበትም። ሙስሊሞች እንደሚያምኑበት ክርስቲያኖችም የሱስን እግዚአብሔር ሳይሞት ወደ ሰማይ ወሰደው ይላሉ። ዳሩ ግን፣ ሁለቱም የሱስ "እንዳልሞተ" ያምናሉ። ለምሣሌ ከሞት በተነሳ ጊዜ ወደ ሰማይ ከማረጉ በፊት ለደቀ መዛሙርቱ መናገሩን መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጻል።
በሱራ 3፡55ና 5፡ 48* "ንፁህ አደርገዋለሁ ተብሎአል" እናም "…አንተ ወደኔ ተመልሰህ ትመጣላህ፤ እኔ(እግዚአብሔር) አንተ ስላልተስማማህበት ጉዳይ ውሳኔ እሰጣለሁኝ" ብሎ ይናገራል። ስለዚህም ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች ከመጣላት ይልቅ ለቀሩት ሚስጥሮች መፍትሄ ለማግኘት መጠበቅ ይኖርባቸው ይሆናል።

ቁርአን ደግሞ የመጨረሻ ፍርድንና የአማኞችን ትንሣኤ ይይዛል (ለምሣሌ ሱራ 36፣77-83፤ ሱራ 69፣13-37፤ ሱራ 75፣99*) የሱስ እንደገና ተመልሶ ይመጣል፣ ለቅዱሳን መጻሕፍት አማኝ ለሆኑ ሰዎች ምስክር ወይም ዳኛ ይሆናል (ሱራ 4፣159፤ ሱራ 16፣89 * ( የሰው ክብር)። እነዚያ - ደግሞ እስላሞች ያልሆኑም-፣ በእግዚአብሔርና በመጨራሻ ፍርድ እንዳለ የሚያምኑና መልካም ሥራ የሚሠሩ ፍርድን መፍራት የለባቸውም (ሱራ 2 ፡ 62፤ሱራ 4፣123-124፤ ከሱራ 7፣170* ጋር ያማሳክሩ)። በቁርአንና በመጽሐፍ ቅዱስም መሠረት፣ ክርስቲያን፣ እስላም ወይም አይሁድም ቢሆኑ፣የመጨራሻ ፍርድ የእግዚአብሔር እንጂ የሰው ሥራ አይደለም። 
( እንደዚያ ዓይነት በሐይማኖት መካከል በሚደረገው ንፅፅር ቁርአን ገለልተኛ ስለመሆኑ ጥርጥር የለውም።)

የሥነ ምግባር መሠረታዊ መርሆዎች

የእነዚህ የሦስቱ የታወቁ የ"አብርሃማዊ ሃይማኖቶች" የሥነ ምግባር መሠረታዊ መርሆዎች* አንዱ ከሌለው ጋር የተያያዙ ናቸው። ትዕዛዛቱ በቁርአንም አሉ፣ ዳሩ ግን በተመሳሳይ መንገድ አልተዘረዘሩም(ለምሣሌ ሱራ 17፣22-39፤ ሱራ 5፣38-40፤ ሱራ 2፣188፤ ሱራ 4፣135፣ ሱራ 2፣195፣ ሱራ 17፣70 *)። ቁርአን ለምሣሌ ማንኛውንም ሰላማዊ ሰው መግደል ሀገወጥ ነው ይላል( ሱራ 5፣27-32*)። ጃሃድ (ግሃድ) ማለት፣ መዋጋት፣ መታገል፣ "የቅዱስ ጦርነት" ትርጉም የተወሰደው ከቁራን ሳይሆን ከመሐመድ አባባሎችና ከእስልምና ህግ ትምህርት ቤቶች ነው***። በውስጥ ሰውነት ወይም በአእምሮና በግብረ ገብነት ከራስ አመጽ ጋር መዋጋት በውጭ ካሉት ከሁሉም ግጭቶች የሚበልጥ "ታላቅ ጂሃድ" ነው ይባላል። መጀመሪያ " በዓይንህ ውስጥ ያለውን ምሶሶ አውጣ" የሚለውን የክርስቶስን አባባል ከዚህ ጋር አወዳድር። በዚህ መንገድ ብዙዎች የውጭ ግጭቶች መሠረታቸው ይላላል። የ "ቃል ጂሃድ" በሰላም ስለአንድ ሰው እምነት መናገር ነው። "የእጅ ጂሃድ" ተንቀሳቃሽ ፣ የአማኙ የማስተማሪያ ምሣሌ ነው። የሰይፍ ጂሃድ" ደግሞም " ትንሹ ጂሃድ" የሚባለው የሚፈቀደው የተጠቃ አማኝን ለመከላከል ብቻ ነው (በቁራን ሱራ 2 ፡ 190* ላይ ካለው ጋር ያገናዝቡ)። ዳሩ ግን ከሌሎች ሃይማኖቶች ጋር በመገናኛት ስለሚከሰተው "ኃይለኛነት" በቁራን ውስጥ ሊገኝ ይችላል (ሱራ 48 ፡ 29 ፤ ሱራ 47፡4*)። ለምሣሌ ያህል ሞስሊም ካልሆነ ሰው ጋር ለመጋባት መከልከልን ጨምሮ የጾታዎችን ግኑኝነት በተመለከተ ሰፋ ያሉ ባህላዊ ህጎች አሉ።

የእስልምና ልምምድ፤ ከእግዚአብሔር ወይም ከአላህ ሌላ እግዚአብሔር የለም እናም መሐመድ የእግዚአብሔር ነብይ ነው፤ የዕለት ተዕለት ፀሎት ይደረጋል ( ሱራ 2፣177*)፤ ዓመታዊ የጾም ወር ወይም ራመዳን ይጠበቃል( ሱራ 2፣ 185*)፤ ቢያንስ በዕድሜ ዘመን አንድ ጊዜ መንፈሳዊ ጉዞ ይደረጋል ( ሱራ 2፣ 196*)እናም "ዘቃት" ወይም የሃይማኖት ሥጦታ ይሰጣል( ሱራ 2፣177*) የሚሉትን ተግባሮች ያጠቃልላል።

በዛሬው እስልምና፣ የሃይማኖት- ስነ ምግባር ጥያቄዎችን የሚወስን ማዕከላዊ ባለሥልጣን የለም። ዳሩ ግን፣ ግልጽ በሆኑ በተከበሩ ምሁራን(ኡላማ) የሚከፈል አቋም በትልቁ ተቀባይነት ያገኛል።

*) ለዚህ ጽሑፍ የጀርመንን ቁርአን - የሩዲ ፓሬትን ትርጉም ተጠቅመናል። በአብዛኛው ጥቅም ላይ የሚውለውን የግብጻውያንንም ቀመር ተጠቅመናል። ሌሎች ትርጉሞች ቁጥሮቹን በተለየ መንገድ ሊቆጥሩ ይችላሉ፤ ከዚያም በዚያው ሱራ ውስጥ የተጠቀሰውን ይዘት ከቁጥሩ በፊት ወይም በፊት ያገኙታል። የቁርአን ምንባቦች ትርጉም ከጀርመን ቁርአንና፣ ትርጉሙ በእስላሞችም ዘንድ ደግሞ ተቀባይነት ካገኘው ከአዴል ቴኦዶር ኮመንተሪ ድጋፍ ተመሳክሮአል (ለምሳሌ በዚያን ጊዜ ዶ/ር እናሙላሂ ከሃን የመለው ዓለም የእስልምና ማህበር ጠቅላይ ጸሐፊ ነበሩ)። የርሳቸው ሀተታ ለእስልምና ት/ቤቶች ባህላዊ አተረጓጎሞች ልዩ ትኩረት ይስጣል። በትክክል ሊረዱት ለሚችሉት ከላይ በተጠቀሱት አካባቢዎች፣ አሮጌውን የአረብኛ የቁርአን ቋንቋ መተርጎም በጭራሽ አስቸጋሪ ነው የሚለው አግባብነት የለውም።

***) የመካከለኛ ዘመን "የመስቀል ጦርነቶችም የሰው ተግባር እንጂ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ አልነበሩም( ለምሣሌ የመስቀል ጦርነቶች በአብዛኛዎቹ በዛሬው የአውሮጳ ክርስቲያኖች ዘንድ መጥፎ ዝና ያለው)።

ወደ ዋናው ገፅ ምረኝ  ways-of-christ.net/am:

ዋናው ጽሑፍ ከተጨማሪ ዐርዕስቶች ጋር (በእንግሊዝኛ):

የየሱስ ክርስቶስ መንገድ፣ እርሱም ለሰብአዊ ፍጡር ልቦና፣ የሰውን ዘርና ምድሪቱን ለመለወጥ የሚያደርጋቸው አስተዋፅዖዎች፤ በበርካታ ምርምርና ልምድ ላይ የተመሠረቱ አዳዲስ አመለካከቶችን በማፍለቅ የግል ባህርይን ዕድገት ለማጎልበት ተግባራዊ የሆነ ጥቆማን የሚሰጥ ገለልተኛ የሆነ የመረጃ ምንጭ ነው።

"የክርስቶስ መንገድ" ድረ ገፅ የምርምርና የጥናት ፕሮጀክት ነው። "የክርስቶስ መንገድ" በሃይማኖቶች መካከል ሰላማዊ ግኑኝነቶችና ጥልቅ መግባባት እንዲኖር ድጋፍ ይሰጣል። "የክርስቶስ መንገድ" ከቤተ ክርስቲያናትና ከሌሎች ድርጅቶች ገለልተኛ ሆኖ ትርፍ ወይም የፖለቲካ ሥልጣን ለማግኘት ጥረት አያደርግም። "የክርስቶስ መንገድ" የሃይማኖት ስብከት እያደረገ ወይም አባላትን ለመሰብሰብ ዘመቻ እያካሄደ አይደለም ያለው።